የእመቤታችን ስደት ታሪክ (ተራኪ ዘላለም ኃይሉ)
Semayat Media Semayat Media
86.1K subscribers
126,814 views
3.8K

 Published On Premiered Oct 27, 2023

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በወርኀ ጽጌ ወደ ግብፅና ኢትዮጵያ ተሰዳ ነበር፡፡ ጌታን ፀንሳ በነበረች ጊዜ ለዮሴፍ አንዳንድ ጊዜ እንደ ጽጌረዳ አበባ ቀይ ሁና፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሮማን አበባ ነጭ ሁና ስትታየው፤ ቀይ የነበረው መልኳ ተለውጦ እንደ ሮማን አበባ ጸዓዳ ነጭ፣ ነጭ የነበረው እንደ ጽጌረዳ ቀይ ሲሆንና የሚያውቀው መልኳ ሲለዋወጥበት ዮሴፍ እየደነገጠ እርሷ መሆኗን ‹‹ማርያም›› እያለ ያረጋገጠጥ ነበር፡፡ (ነገረ ማርያም) ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ‹‹የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም›› ያለውን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲተረጉመው ‹‹መልኳ እንደ ጽጌረዳና እንደ ሮማን አበባ ይለዋወጥበት ስለነበር በአንድ ዓይነት መልክ አላወቃትም›› ብሏል፡፡ (ማቴ. ፩፥፳፭) ያንን ለማውሳት ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለው ወቅት ወርኀ ጽጌ ተባለ፡፡

show more

Share/Embed